የተወደዳችሁ የቤተሰብ ማህበር አባሎች እንኳን ደህና ቆያችሁን!

በ Covid-19 ምክንያትና እሱን ተከትሎ በመጣው የሁሉም መዘጋጋት፣ ምንም እንኳን ለማድረግ እና ለመፈጸም ያቀድናቸውን ተግባራቶች መቶ በመቶ ለመከወን ባንችልም፣ የቤተሰብ ማህበር የቦርድ አባሎች ደከመኝና ሰለቸኝ ሳንል ያደረግናቸውንና በማከናወንም ላይ ያለናቸውን አብይት ነጥቦች ለእናንተ ለአባሎቻችን ለማሳወቅ እና ለማስተዋወቅ  እንወዳለን። እነዚህ እሴቶች አሁንም ሙሉ በሙሉ እንዲሳኩ አሁንም በተጠናከረ ሁኔታ ከእናንተ ህብረት እና ጥረት ጋር እንደምናሳካቸው ምንም ጥርጥር የለንም።

1ኛ   ስለ Covid-19 መረጃ በተለይ ላይፕዚግን ሚመለከቱ የመንግስት መመሪያዎችን እየተከታተልን በድህረገጽችን፣ በፌስቡክ እና በትዊተር በአማርኛ ስናቀርብ ነበር። 

2ኛ   Covid-19 ን ተከትሎ ህዝባችንን እና ወገናችንን ለመርዳት በሚል ባደረግነው የሁላችንም ጥረት የተሰባሰበውን 2.520,00€ ወይም 2.623.00$ ለዚህ አላማ ገቢ ከሚያሰባስቡት ድርጅቶች ውስጥ በ Global Alliance Fort the Rights of Ethiopians የከፈተውን ጎ-ፈንድ-ሚ አካውንት Support Ethiopians against COVID-19 ውስጥ በማስገባት የዜጎቻችንን ችግር በመጠኑም ለመቅረፍ በመቻላችን ኩራት ቢሰማንም አሁንም ግን ማሰስባሰባችንን እንደቀጠልን መሆናችንን ለማሳወቅ እንወዳለን።ኮሮና አሁንም አለና። 

3ኛ   በማህበራችን ደንብ ላይ እንደ ዋና ነጥብ አድርገን ያስቀመጥነው የጀርመንኛ ቋንቋን ለመማር ለሚፈልጉ አባሎቻችን ሁኔታዎችን ማመቻቸት መሆኑ የሚታወስ ነው። ይህንንም በተመለከተ ከ Villa- Leipzig.de (የተለያዩ በጎ አድራጊ ድርጅቶችን በስሩ የያዘ) ማህበር በመነጋገር በተለያዩ ደረጃዎች ከ A1 አንስቶ እስከ B2 ድረስ የቋንቋ ትምህርት የሚገኝበትና ከዚህም አልፎ ለፈተና አዘጋጅቶ ለማቅረብ ጥረት በማድረግ ላይ የምንገኝ ስንሆን ከላይ እንደተጠቅሰው አንድም በኮሮና የተነሳ ሁለትም አሁን የበጋ እረፍት Sommerferien በመሆኑ ውሳኔውን የሚወስኑት አካሎች ለጊዜው ስራ ላይ ባይገኙም ወደ ስራ ገበታቸው ሲመለሱ የኛን ጉዳያችን አይተው የሚያሳውቁንን ወደ እናንተ የምናደርሰው ይሆናል። እስከዛው ድረስ ግን ሁሉም የማህበራችን አባሎች ከሰኞ እስከ አርብ በቀን በተለያዩ ሶስት ፕሮግራሞች ትምህርት መውሰድ እንደሚችሉ ስናሳውቅ በደስታ ነው። ይህም ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት የማያስፈልገው ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ደርጃዎች ስር የሚሰጥ በመሆኑ ማናችንንም ለማሳተፍ የሚችለድል ነው። ቦታውና የሰአቱ ፕሮግራም እንደሚከተለው ነው፤

4ኛ   አሁን እንደሚታወቀው ትምህርት ቤት ዝግ መሆኑና ለተማሪዎች የእረፍት ጊዜ በመሆኑ ለአባሎቻችንና በተለይም ለልጆቻችን የመዝናኛ ፕሮግራም በማቀናጀት ጥረት Leipziger Zoo በመጎብኘት የተለየ የመዝናናትና የመማር እድል እንዲያገኙ በማህበራችን ስም እየሞከርን  ያለውን ሂደት በቅርቡ መልስ ሲያገኝ እንዴትና በምን አይነት ሁኔታ ይኽንን ቀን እንደምናሳልፍ ከእናንተ ጋር በአንድነት የምንወጥነው ይሆናል። ያም ማለት ምን ያህል ሰው እና አከፋፈሉንም ይመለከታል።

5ኛ   ምንም እንኳን በኮሮና ምክንያት እና በስራ ተወጥረን ያለ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን መርዳት እና ከጎናቸው ለመቆም ባለን ጽኑ ፍላጎት ለጊዜው በህክምና ላይ የሚገኝ ወይም ምትገኝ አንድ ወንድማችን ወይም እህታችንን 120 ኪሜ እየተጓጓዝን በየጊዘው እየተቀያየርን (ከቦርድ አባል ውጪ የሆኑ አባላቶቻችንንም እየጨመርን) በመመላለስ ደህንነቱን ወይም ደህንነቷን በመጠየቅና ከ ሃኪሞቹ ጋር በመነጋገር ብቻውን አለመእሆኑን ወይም ብቻዋን አለመሆኗን በማሳየት ላይ እንገኛለን። ይኼም ማለት ሁላችንም እንደ ቤተሰብ የምንጠያየቅ፣ የምንተሳሰብና አንዳችን ለሌላችን ደህንነት አብረን የምንቆም እንደመሆናችን የቦርዱ አባላት ብቻ ሳንሆን ሁላችንንም አሳትፎ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን የምንንከባከብበት ሁኔታዎችን መፍጠር አስፈላጊ ነው። እስካሁንም የዘነጋናቸውና ትኩረት ያልሰጠናቸው የሚመስላቸው ወዳጆቻችንን ከውዲሁ ይቅርታ እየጠየቅን እርስ በእርስ በመነጋገርና በማስታወስ ሁሉንም የሚያሳትፍ መድረክ ለመክፈት ጥረታችን አሁንም ይቀጥላል።

6ኛ አስደሳች ዜና! የዘመን መለወጫ እንቁጣጣሽን በአንድነትና በደስታ ለማክበር በፈረንጆች አቆጣጠር September 11 2020 (አርብ) ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ የምንገኝ ሲሆን በቅርቡ ሁላችንንም የሚያሳትፍ እና የኛ የምንለውን ዝግጅት የምንፈጽምበትን ቦታና ዝርዝር ሁኔታዎችን እንደምናሳውቃችሁ ስንገልጽ በደስታ ነው።

ሃገራችንንና ህዝባችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን

ቤተሰብ ለዘላለም!