BETESEB - Äthiopier und Freunde Äthiopiens e.V., Leipzig
ቤተሰብ - ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር በላይፕዚግ
BETESEB - Ethiopian and Friends of Ethiopia Community, Leipzig
Willkomen! እንኳን ደህና መጡ

Suche:
እንኳን አደረሳችሁ አደረስን!
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ አደረስን::
በዓሉን የሰላም አና የፍቅር ያድርግልን!
መልካም የትንሳኤ በዓል!
BETESEB Admin / 05.05.2024   
እንኳን አደረሳችሁ አደረስን! ዒድ ሙባረክ!
እንኳን አደረሳችሁ አደረስን! ዒድ ሙባረክ!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445 ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ እደረሰን።
በዓሉን የሰላም አና የፍቅር ያድርግልን!
BETESEB Admin / 10.04.2024   
መልካም የከተራና የጥምቀት በዓል!

ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

መልካም የከተራና የጥምቀት በዓል!

BETESEB Admin / 19.01.2023   
9-Euro-Ticket / የ9-ዩሮ-ትኬት
በዩክሬን ጦርነት ምክንያት የነዳጅ እና የናፍታ ዋጋ በጣም ሰለጨመረ የጀርመን ፌደራል መንግስት በ 9-ዩሮ ትኬት ዜጎችን መደገፍ እና ዜጎች ከመኪና ወደ ህዝብ ትራንስፖርት መቀየርን ቀላል ማድረግ ይፈልጋል። በዚህ ትኬት 9€ ከፍለው ለአንድ ወር በመላው ጀርመን  መጓዝ ይችላሉ። ትኬቱ መቼ አና የት ነው የሚገኘው? ትኬቱን... mehr»
Admin BETESEB / 27.05.2022   
እንኳን ለኢድ አልፈጥር በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🙏🏾

የተከበራችሁ የእስልምና ኃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ፥
እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልን በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር አና የአብሮንት እንዲሆን እንመኛለን።

Anteneh Mamo / 01.05.2022   
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🙏🏾
የተከበራችሁ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን አና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣
እንኳዋን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልን፤ 
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር አና የአብሮንት እንዲሆን እንመኛለን።
Anteneh Mamo / 23.04.2022   
እንኩዋን ለጥምቀት በአል አደረሳችሁ አደረሰን🙏🏾

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኩዋን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እያልን: በአሉ የሰላም የፍቅር የደስታ እና የአንድነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ልጆቹዋን ይባርክ!

BETESEB Admin / 18.01.2022   
መልካም አዲስ አመት 2022

መልካም አዲስ አመት!!
Gesundes Neues Jahr!!
Happy new year!!

እንኩዋን ለ 2022 አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

አመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳስብ ይሁንልን። አሜን!

BETESEB Admin / 31.12.2021   
እንኩዋን ለመውሊድ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ለመላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን::

በአሉ የሰላም የጤና፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

BETESEB Admin / 17.10.2021   
መዋጮውን አስተላልፈናል!

BETESEB Admin / 10.10.2021   
እናመሰግናለን 🙏🏽

BETESEB Admin / 10.10.2021   
ወገን ለወገን ጥሪ

BETESEB Admin / 30.09.2021   
እንኳን ለብርሃነ መስቀል አደረሳችሁ አደረሰን

እንኳን ለመስቀል ደመራ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን::

በአሉ የሰላም: የአንድነት እና የመተሳሰብ ያድርግልን ዘንድ ከልብ እንመኛለን::

በአሉ ስናከብር በሃዘን ውስጥያሉ : በችግር ላይ የወደቁ ዜጎቻችንንእያሰብን ለሃገራችን እና ለሃገራችን ህዝብ ሁሉ ዘላቂ ስላም እንዲሰጠን ፈጣሪያችንን እየተማፀንን እንዲሁም አደራ እንላለን::

BETESEB Admin / 27.09.2021   
መልካም አዲስ አመት 2014 Happy Ethiopian New Year 2014

ለመላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፡

እንኳን ለአዲሱ አመት 2014 በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

መጪው አዲስ አመት የጤና የሰላምና የፍቅር እንዲሆን እንመኛለን። 
ከሁሉም በላይ ደግሞ አገራችን ኢትዮጽያም ሰላም እና አንድነትን የምትታይበት ዓመት ያድርግልን።
 
BETESEB Admin / 11.09.2021   
እንቁጣጣሽን አንድ ላይ እናክብር!

BETESEB Admin / 01.09.2021   
እንኳ ለኢድ አል-አዳሐ በአል አደረሳችሁ! አደረሰን!

ለመላው እስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው አመት ሒጅራ የኢድ አል-አዳሐ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።

በአሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን።

BETESEB Admin / 20.07.2021   
መልካም ኢድ አልፈጥር!

ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ ለ 1442 ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

እያልን መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እንዲሁም የአብሮነር ያርግልን።

መልካም ኢድ አልፈጥር!

BETESEB Admin / 12.05.2021   
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን አና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፤

እንኳዋን ለብርሃነ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን እያልን 

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር አና የአብሮንት እንዲሆን እንመኛለን።

BETESEB Admin / 01.05.2021   
ከነገ ጀምሮ አዲሱ የኮሮና መከላከያ ደንብ (Bundes-Notbremse) ላይፕዚግ ላይ ይሰራል

ከነገ 24.04.2021 ጀምሮ በአዲሱ የኮሮና መከላከያ ደንብ (Bundes-Notbremse) መሰረት Sachsen ውስጥ የኮሮና  የቁጥጥር  እርምጃ  ስራ ላይ ይውላል፣ በላይፕዚሽም  እንዲሁ።   

ከመቶ ሺህ ስንት አዲስ  ኢንፌክሽን (Infektion) በሰባት ቀን ውስጥ እንዳለ የሚያሳየውን (Incidenz) ተከትሎ ህጎቹ ይጠብቃሉ  ወይም ይላላሉ።

ዛሬ 23.04.2021 ላይፕዚግ  ኢንሲደንዙ 121,9  ነው። ስለዚህ ከነገ 24.04.2021 ጀምሮ፤  

  • መገናኘት የሚቻለው ከራስ ቤተሰብ ሌላ ከአንድ  ሰው  ጋር ብቻ ነው (ልጆች እስከ 14 አመት ድረስ አይቆጠሩም)   
  • ከለሊቱ አራት ሰአት እስከ ንጋቱ 11 ሰአት (22-5 Uhr) ለስራ  ምክንያት ካልሆነ ቤት ለቆ መውጣት አይፈቀድም      
  • ለህይወት  በጣም ከሚያስፈልጉ ነገሮች በቀር (Grundversorgung) ኢንሲደንዙ  150 እስኪሞላ ድረስ  ሌሎች ሱቆችም  በ click and meet  ማለትም  Einkaufen mit Termin  ማለትም ግዢ በቀጠሮ  ይቻላል።ለዚህ ግን  ወቅታዊ የሆነ ይኮሮና ኔጋቲቭ  ቴስት ያስፈልጋል። ቴስቱንም  ለሁሉም ዜጋ  በሳምንት አንዴ በነጻ  በተለያየ  Testzentren ለምሳሌ  ባንሆፍ  ውስጥ  ማሰራት ይቻላል። ሚያገለግለው  ለ24 ሰአት ነው።
  • ት/ቤት በ Wechselmodell ማለትም  ተከፋፍሎ ይከፈታል። ሆኖም ኢንሲደንዙ  ከ 165 ካለፈ ት/ቤቶችም ይዘጋሉ። በተረፈ ሌላው ባለበት ይቀጥላል።

ስለዚህ  ኢንሲደንሱን  በየጊዜው መከታተል ጠቃሚ ነው።

BETESEB Admin / 23.04.2021   
እንኳን ለ1442ኛው ረመዳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ውድ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን አና የኢትዮጵያ ወዳጆች፣
ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፤
 
ረመዳኑ የፍቅር፣ የሰላም፣ የአንድነት አና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንዲሆንልን እንመኛለን!
 
ረመዳን ከሪም!
BETESEB Admin / 13.04.2021   
እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ አደረሰን 🙏🏾

እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ እያልን፤

ለበዓሉ ጊዜ ብሎም በቀጣይነት ለሁላችንም በያለንብት እንዲሁም ለሃገራችን ሰላም፣ ጤንነት፣ ፍቅር እና አብሮነትን እንመኛለን። 

 
መልካም ገና
ፈጣሪ ሃገራችንን ይጠብቅልን!
 
 
BETESEB Admin / 06.01.2021   
እንኳን ለአዲሱ አመት 2021 ዓ/ም አደረሳችሁ አደረሰን

እንኳን ለጎርጎሮሳውያኑ 2021 ዓ/ም በሰላምና በጤና ጠብቆ አደረሳችሁ አደረሰን እያልን:

ዓመቱ የሰላም: የጤና: የስኬት እንዲሁም ዓለማችን ከኮሮና ነፃ ሆና ጤንነት ሰፍኖ ወደ ቀድሞ ኑሯችን የምንመለስበት: ሀገራችንም ሰላሟ ሰፍኖ ህዝቦቿ በሰላም ወተው የሚገቡበት: ሰብሎቿ አምረው አውድማ ጎተራዋን ሞልቶ: ረሀብ እና መፈናቀል ቀርቶ የጥጋብ እና የተትረፈረፈ የምርት ዘመን ይሁን በማለት መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን::

መልካም አዲስ ዓመት 🍾

 

BETESEB Admin / 31.12.2020   
BLACK DAY

BETESEB Admin / 03.11.2020   
ከ Noverber 2 2020 ጀምሮ ተጨማሪ የኮሮና መመሪያዎች በመላው ጀርመን ይተገበራሉ፤

Noverber 2 2020 ጀምሮ ተጨማሪ የኮሮና ደንቦች በመላው ጀርመን ይተገበራሉ፤

- አደባባይም ሆነ በቤት ውስጥ የሁለት ቤተሰብ አባላቶች ብቻ፣ በቁጥር 10 የማይበልጡ መገናኘት ይችላሉ። ቤት ውስጥ ፓርቲ ማድረግ አይፈቀድም።

- ምግብ ቤቶች፣ቡና ቤቶች፣ክለቦች፣ዲስኮዎች፣መጠጥቤቶች እና መሰል ተቋማት ይዘጋሉ። ወደ ቤት ይዞ ሚኬድ ምግብ ግን መሸጥ ይችላል።

- ሱቆች አና ገበያዎች ክፍት ሆኖ ይቀጥላል። ውስጥ ግን  በ 10 ካሬ ሜትር የሽያጭ ቦታ ከአንድ ደንበኛ በላይ አለመኖሩን መረጋገጥ አለበት።

- ትምህርት ቤቶች እና መዋእለ ህጻናት ክፍት ሆነው ይቀራሉ።

- ሆቴሎች እና ማደሪያ ቤቶች ለጊዜው ምንም የቱሪስትማረፊያ አይሰጥም። ዜጎች ከግል ጉዞዎች፣ ከቀን ጉዞዎች እና ከዘመዶች ጉብኝቶች መቆጠብ አለባቸው።

- መዝናኛ ቤቶች እንደ ፊልም፣ ቲያትር፣ ኦፔራ እና ኮንሰርት ቤቶች እና መሰል ተቋማት ይዘጋሉ።

- ስፖርት እና መዋኛ ቤቶች ይዘጋሉ። የግል ስፖርት ለሁለት ወይም ከቤተሰብ አባልጋር ይቻላል። የፕሮፊ የስፖርት እንደ ቡንደስሊጋ አይነት ያለ ተመልካቾች ሊከናወኑ ይችላሉ።

- የቆንጅና ሳሎኖች፣ ማሳጀ ቤቶት፣ ንቅሳት ስቱዲዮዎች እና የመሳሰሉት ይዘጋሉ።

- የኢንፌክሽን መከላከያ መስፈርቶች እስከተሟሉ ድረስ የቤተክርስቲያንእናየጸሎትዝግጅቶች ሊከናወኑ ይችላሉ።
BETESEB Admin / 30.10.2020   
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን✝️

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን በሙሉ፤

እንኩዋን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!🙏🏽

በአሉ የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የመቻቻል እንዲሆንልን እንመኛለን። ፈጣሪ አገራችን ኢትዮጵያንን ሰላም ያርግልን፣ ይጠብቅልን።

መልካም በአል🙏🏽

  

BETESEB Admin / 27.09.2020   
መልካም አዲስ አመት 2013

BETESEB Admin / 11.09.2020   
መልካም አዲስ አመት 2013 !!

መልካም አዲስ አመት!

የጎመን ምንቸት ውጣ የስጋ ምንቸት ግባ!

2013 የሰላም፣ የጤና፣ የአንድነት፣ የብልፅግ እና የስኬት እንዲሁም የፍቅር ዘመን እንዲሆንልን ስንል እንመኛለን።

ባለፈው አመት በቆሰልንባቸው፣ ባዘንባቸው ሁሉ የምናገግም፣ አገራችን የሰላም አየር የምትተነፍስበት፣ ለእርቅ፣ ለውይይት የምንቀመጥበት፣ የስራ፣ የእድሳት አመት ይሁንልን።

እዚህ ያደረሰን ፈጣሪያችን ክብር ምስጋና ይግባውና በአዲሱ አመት ይህንን ክፉ ጊዜ ከቁጥር ሳያጎለን አሻግሮ እንደዚህ ለመሰባሰብ ያብቃን!!

መልካም አዲስ አመት ለሁላችን።

BETESEB Admin / 10.09.2020   
የእንቁጣጣሽ በአል ዝግጅታችንን ለማዘዋወር ተገድናል

የተወደዳችሁ የቤተሰብ አባሎች

የዘመን መለወጫ እንቁጣጣሽ በአልን አንድ ላይ እንደ ቤተሰብ ከሌላው ጊዜ በተለየ በሃገራችን ወግ እና ደንብ አብረን ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶችን ከማከናወን ባሻገር ቦታውንም መርጠን የግብዣ ጥሪ ለመላክ በምንሰናዳበት በዚህ ወቅት በተለያዩ የጀርመን ክልሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያሻቀበ የመጣው የ COVID19 አዲስ የተያዙ በሽተኞች ቁጥር ነገሩን ረጋ ብለን እንድናስታውል ግድ ብሎናል።

በዚህም መሰረት ለጊዜያዊ ደስታ ስንል የምንወዳቸውን የቤተስብ አብሎቻችን እና ቤተስቦቻቸውን ለዚህ አደጋ ከምናጋልጥ የበአሉን ዝግጅት ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉ ይሻላል በሚል ውሳኔ ስለተስማማን፣ ምንም እንኳን ልባችን ቢያዝንም ከራሳችን እና ከልጆቻችን ጤንነት የሚበልጥ ነገር ስለሌለ ሁኔታው ሲረጋጋ በተሻለና በሚያስጎመጅ መልኩ እንደምናከብር ከወዲሁ ቃል እንገባለን።

ሰላምና ጤና ለሁላችን! ሃገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!

የቤተሰብ ቦርድ 

BETESEB Admin / 30.08.2020   
Leipziger Zoo ጉብኝት ከልጆች ጋር

BETESEB Admin / 20.08.2020   

 

BETESEB Admin / 20.08.2020   
የጊዜ ሰሌዳ Leipziger Zoo
የተወደዳችሁ የ ቤተሰብ አባሎችና ወዳጆች፣ የነገውን የ Leipziger Zoo ጉብኝት ፕሮግራም ግብዣን ጥሪ ተከትላችሁ ክልጆቻችሁ ጋር ወይም ከልጆቻችሁ ጎዋደኞች ጋር ለመምጣት በመወሰናችሁ የሚሰማንን ደስታ በማህበራችን ስም እየገለጽን ይህ ቀን ለሁላችንም በተለይ ለልጆቻችን የማይረሳ ክስተት እንዲሆን... mehr»
BETESEB Admin / 14.08.2020   
የምስራች ለልጆች!
የምስራች ለልጆች! ውድ እና የተከበራችሁ የበተሰብ ማህበር አባሎች እንደምን... mehr»
BETESEB Admin / 10.08.2020   
ዒድ ሙባረክ!
ዒድ ሙባረክ! ለመላው የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንኳን ለ1441ኛውና ለታላቁ የዒድ አል-አድሐ (አረፋ) በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ለማለት እንወዳለን። በአሉ የሰላም፣ የፍቅት፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ ከልብ እንመኛለን! በዚህ አጋጣሚ... mehr»
BETESEB Admin / 30.07.2020   
የተወደዳችሁ የቤተሰብ ማህበር አባሎች እንኳን ደህና ቆያችሁን!
የተወደዳችሁ የቤተሰብ ማህበር አባሎች እንኳን ደህና ቆያችሁን! በ Covid-19 ምክንያትና እሱን ተከትሎ በመጣው የሁሉም መዘጋጋት፣ ምንም እንኳን ለማድረግ እና ለመፈጸም ያቀድናቸውን ተግባራቶች መቶ በመቶ ለመከወን ባንችልም፣ የቤተሰብ ማህበር የቦርድ አባሎች ደከመኝና ሰለቸኝ ሳንል ያደረግናቸውንና... mehr»
BETESEB Admin / 22.07.2020   
ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በ ፍራንክፉርት !
BETESEB Admin / 14.07.2020   
ለውድ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ፤
በላይፕዚግ ከተማ የሚገኘው ቤተሰብ የኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ሃዘን ይገልጻል፣ እንገልጻለን። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎቻችንና ወገኖቻችን በተለይም ህጻናት እና እናቶቻችን... mehr»
BETESEB Admin / 07.07.2020   
ዛሬን 06.06.2020 ን ጨምሮ 2.623,00$ ወይም 2.514,79€ አሰባስበን አስተላልፈናል
ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለምታደርጉት አስተዋጽኦ እያመሰገንን፣ እስካሁን ከእኛ እና ከእናንተ በአጠቃላይ 2.623,00$ ወይም 2.514,79€ አሰባስበን አስተላልፈናል።   mehr»
BETESEB Admin / 06.06.2020   
እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድም እህቶቻችን በሙሉ እንኳን 1441ኛው ታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት ቤተሰብ - ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር መልካም ምኞቱን እየገለፀ፤ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የብልፅግና፣ የመተሳሰብ እና የተቸገሩ... mehr»
BETESEB Admin / 23.05.2020   
ዛሬን 10.05.2020 ን ጨምሮ 2.258,00$ ወይም 2.175,3€ አሰባስበን አስተላልፈናል
ዛሬን ጨምሮ 2.258,00$ ወይም 2.175,3€ አሰባስበን አስተላልፈናል።  እሁንም አሰባስቦ ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን። mehr»
BETESEB Admin / 10.05.2020   
ከዛሬው ከ 04.05.2020 ጋር እስካሁን 2.058,00$ ወይም 1.982,61€ አሰባስበን አስተላልፈናል
እስካሁን 2.058,00$ ወይም 1.982,61€አሰባስበን አስተላልፈናል፣ አሁንም ማሰባሰቡን አና ማስተላለፋን እንቀጥላለን።  mehr»
BETESEB Admin / 04.05.2020   
እስካሁን በማህበሩ ስም 1.908,00$ ወይም 1.839,71€ ሰብስበን አስተላልፈናል
ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለምታደርጉት አስተዋጽኦ እሁንም በድጋሚ እያመሰገንን፣ ዛሬም ከእናንተ ያሰባሰብነውን አስተላልፈን። እስካሁን 1.908,00$ ወይም 1.839,71€ አሰባስበን አስተላልፈናል። እሁንም ለእርስዎ በእርሶዎ ስም ወይም በማህበሩ ስም መዋጮዎን ማሰባሰባችንን እና ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን።       mehr»
BETESEB Admin / 01.05.2020   
እስካሁን በማህበሩ ስም 1.778,00$ ወይም 1.714,72€ ሰብስበን አስተላልፈናል
ጥሪያችንን ሰምታችሁ ለምታደርጉት አስተዋጽኦ በድጋሚ ከልብ እያመሰገንን፣... mehr»
BETESEB Admin / 29.04.2020   
እስካሁን በማህበሩ ስም 1.628,00$ ወይም 1.454,09€ ሰብስበን አስተላልፈናል
ውድ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤ ጥሪያችንን ሰምታችሁ ስላደረጋችሁት አስተዋጽኦ ከልብ እያመሰገንን፣ እስክሁን በቀጥታ ሊንኩ ሳይሆን በማህበሩ ስም 1.628,00$ ወይም 1.454,09€ ሰብስበን አስተላልፈናል። እሁንም ለእርስዎ በእርሶዎ ስም ወይም በማህበሩ ስም መዋጮዎን ማሰባሰባችን እና... mehr»
BETESEB Admin / 28.04.2020   
ሮመዳን ከሪም🌙

ለውድ ሙስሊም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በሙሉ መልካም የፆም የፀሎት ወር ይሁንላችሁ።

ፆሙን የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ያርግልን። እንዲሁም ከዘመን አመጣሽ በሽታ እንዲጠብቀን ወደ አምላክ ዱአ የምናደርግበት የምናደርግበት ይሁን።

BETESEB Admin / 25.04.2020   
የኮሮናን ቫይረስን ለመከላከል የገቢ ማሰባሰቢያ ላይ መሳተፍ
የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች፤ በአሁን ሰአት በአለማችን ላይ የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በሃገራችን እንደገባ እና በቫይረሱ ዜጎች እየተጠቁ እንዲሁም ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በሽታውን ለመከላከል ሲባል... mehr»
BETESEB Admin / 22.04.2020   
እንኩዋን አደረሳችሁ አደረሰን 🙏🏾

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንክዋን ለብርሃነ ትንሳኤ በስላም አደረሳቹ አደረስን እያልን በአሉ የስላም የፍቅር የአብሮንት በጋራ የምንተጋገዝበት እንዲሆን እንመኛለን::

BETESEB Admin / 19.04.2020   
ከሰኞ ጀምሮ ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ የአፍ እና የአፍንጫ ጭንብል ግዴታ ነው!
ከሰኞ April 20 2020 ጀምሮ እስከ Mai 3 2020 ድረስ የጀርመን ግዛት ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ በህዝብ መጓጓዣ እና ሱቆች ውስጥ አፍ እና አፍንጫ መሸፈን ግዴታ ነው። አፍ እና አፍንጫ መሸፈኛው ጭንብል የግዴታ ውዱ FFP2-ማስከ መሆን የለበትም፣ ቀላል ጨርቅ ውይም ሻል መሆን ይችላል። በተጨማሪ የቤተክርስቲያን እገልግሎቶችም... mehr»
BETESEB Admin / 17.04.2020   
የኮሮና መስፋፋትን ለመቀነስ የወጣው መመሪያ እስክ Mai 3 ተራዝሟል
የኮሮና መስፋፋትን ለመቀነስ የወጣው መመሪያ እስክ Mai 3 ተራዝሟል! ላይፕዚግን ጨምሮ በፈዴራል ግዛት ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ በአሁኑ ሰአት የሚሰራው „ከቤት ያለመውጣት መመሪያ“ (Ausgangssperre bzw. -beschränkungen) ከ ሰኞ April 20 2020 ጅምሮ ይነሳል። ያማለት ከ ሰኞ ጀምሮ ቤት ለቆ ለመውጣት ምክንያት አያስፈልግም። በአገር ደረጃ... mehr»
BETESEB Admin / 16.04.2020   
ቤተሰብ AmazonSmile ፕሮግራም ውስጥ ገብቷል
የአማዞን (Amazon) ደንበኛ ነዎት? ከሆነ በሚቀጥለው ግዥዎ ለእኛ አንድ ጥሩ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፤ በ AmazonSmile በኩል ይግዙ!  AmazonSmile ለአማዞን ደንበኞች ቀላሉ መንገድ ነው፣ ከእያንዳንዱ ግዢ ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በጎ አድራጊ ድረጅቶችን መርዳት የሚችሉበት። የኛ ማህበር "ቤተሰብ - የኢትዮጵያዊያን እና... mehr»
BETESEB Admin / 02.04.2020   
ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ ከቤት አለመውጣት መመሪያ እስከ April 20
በላይፕዚግ ብሎም ባጠቃላይ ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ አሁን የሚሰራው ከቤት አለመውጣት መመሪያ (Ausgangsbeschränkung) እስከ April 20 ተራዝሟል። ስለ ክልከላው ተጨማሪ መረጃ በ 22.03.2020 ያቀረብነውን "ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ ላይፕዚሽ ውስጥ ከቤት መውጣት ክልክል ነው" ይመልከቱ። mehr»
BETESEB Admin / 01.04.2020   
ስለ ኮቪድ-19 (COVID-19) ቫይረስ:
↪️ቫይረሱ በስብ(Fat) የተሸፈነ ነው፡፡ ↪️በአይን፣ በአፍንጫ ወይም ወደ አፍ በመግባት ልያጠቃን ይችላል፡፡ ↪️ቫይረሱ የፕሮቲን ሞሊኪዩል በመያዙ የሚሞት ሳይሆን በራሱ ጊዜ የሚሟሽሽ ነው፡፡ የሚጠፋበትም ጊዜ የሚወሰነው በአካባቢው ባለው የሙቀትና የአየሩ እርጥበት መጠን እንዲሁም... mehr»
BETESEB Admin / 01.04.2020   
ጸረ ኮሮና አፕ (Anti Corna App) ምንድን ነው?
ጸረ ኮሮና አፕ (Anti Corna App) ጀርመን ውስጥ "ገና" አልተፈቀደም። በ የውሂብ ጥበቃ (Datenschutz / Data protection) ምክንያት ገና እየተወያዩበት ነው። ከተፈቀደም በፍላጎት ላይ የተመስረተ መሆን አለበት ባዮች ብዙ ናቸው:: የሚሰራው እደዚ ነው፤ ሞባይልሽ በብሉቱዝ  (Buetooth) በአንድ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኙ ሌሎች  ሞባይሎች ጋር... mehr»
BETESEB Admin / 30.03.2020   
ከቤት መውጣት ክልከላ (Ausgangssperre) እና የግንኙነት ክልከላ (Kontaktverbot)
ጀርመን ውስጥ ሁሉም ቦታ ያለ በቂ ምክንያት ከቤት መውጣት ተከልክሏልን (Ausgangssperee) ? ሁሉም ቦታ አልተከለከልም። ከዛክሰን (Sachsen) ውጪ በአሁን ሰአት Bayern፣  Mecklenburg-Vorpommern እና Saarland ያለ በቂ ምክንያት ከቤት መውጣት ተከልክሏል፣ ሌሎች የፌዴራል ግዛቶች ግን እስካሁን አልከለከሉም ። ግን! ከ23.03.20 ጀምሮ በአጠቃላይ በጀርመን... mehr»
BETESEB Admin / 23.03.2020   
ከዛሬ ሌሊት ጀምሮ ላይፕዚሽ ውስጥ ከቤት መውጣት ክልክል ነው
እንደተጠበቀው ዛክሰን (Sachsen) ውስጥ ላይፕዚሽን ጨምሮ ከዛሬ እሁድ ሌሊት ጀምሮ ያለ በቂ ምክንያት ከቤት መውጣት የተከለከለ ነው። መከልከሉ በመጀምሪያ ለ 14 ቀን ይሰራል፡፡ በዚህ ሰአት ከቤት ለመውጣት እንደ ብቂ ምክንያት ሚቆጠሩት፤ በህይወት እና በንብረት ላይ የመጣ አደጋን ለመሸሽ ወደ ስራ... mehr»
BETESEB Admin / 22.03.2020   
የኮሮና ቫይረስን ለመግታት በላይፕዚግ የተወሰኑ ድንጋጌዎች
የኮሮና ቫይረስ መስፋፋትን ለማገድ የጀርመን ፌዴራል መንግስት እና የፌዴራል ግዛቶች ብሎም በከተማ ደረጃ የተለያዩ ውሳኔዎችን ይተላልፋሉ። ለምሳሌ ባየርን (Bayern) ወይም ድሬስደን (Dresden) በአጠቃላይ ወደውጪ መውጣት ሲከለክል (Ausgangssperre)፣ ላይፕዚግ (Leipzig) ደሞ ሰዉ በፈቃደኝነት ከቤት እንዳይወጣ ይመከራል። በላይፕዚግ... mehr»
Anteneh Mamo / 21.03.2020   
ለ ዳግማዊ ትንሳኤ የታቀደው ዝግጅት ተሰረዘ

ለ ዳግማዊ ትንሳኤ ዋዜማ በ 25. April 2020 አቅደነው የነበረው ዝግጅት ከአቅማችን በላይ በሆነው በወቅታዊው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተሰርዟል።

 Die für April 25. April 2020 geplante Veranstaltung müssen wir leider wegen der Ausbreitung des Coronavirus absagen.

Anteneh Mamo / 16.03.2020   
የ ቤተሰብ መጀመሪያ ዝግጅት

ቤተሰብ - ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር

የመጀመሪያ ዝግጅት ለ ዳግማዊ ትንሳኤ ዋዜማ በ 25.04.2020

BasaMo Insel . Odermannstraße 8 . Leipzig

 Die erste Veranstaltung von

BETESEB - Äthiopier und Freunde Äthiopiens e.V.

am 25.04.2020 in BasaMo Insel . Odermannstraße 8 . Leipzig

02.03.2020   
ቤተሰብ ህጋዊ ሰውነት አገኘ

ቤተሰብ - ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር 

ከ 25.02.2020 ጀምሮ ህጋዊ ሰውነት አግኝቷል።


BETESEB - Äthiopier und Freunde Äthiopiens e.V.

wurde am 25.02.2020 im Register des Amtsgerichtes Leipzig eigetragn.

 

Amtsgericht Leipzig: VR 9629 ▪ Steuernummer: 232/140/19396

BETESEB Admin / 25.02.2020   
ቤተሰብ ማህበር ተቋቋመ

እንድኳዋን ደስ አለን! 

ቤተሰብ - ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ማህበር

በእለተ 22.12.2019 ላይፕዚግ ውስጥ ተቋቋመ 

  

BETESEB - Äthiopier und Freunde Äthiopiens e.V.

wurde am 22.12.2019 gegründet

BETESEB Admin / 22.12.2019   
የመጀመሪያው እንተዋወቅ ስብሰባ
BETESEB Admin / 30.11.2019